በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቡሬ ከተማ የዕድገት በአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒዩን ኃ.የተ ሎት 1 የጽህፈትና ቢሮ አስተዳድር የሚሆኑ የፕሪንተር ቀለም፣ የፎቶ ኮፒ ቀለም፣ ቢክ እስክርቢቶ፣ ኬንት፣ የኮምፒውተር ወረቀት፣ ፓርከር፣ የማህተም ቀለም፣ ካርቦን የእስቴፕላር ሽቦ፣ ማስታወሻ ደብተር እና ቀለም፣ የሒሳብ ቋት፣ ፋስትነር፣ ሎት 2 ህትመት ማለትም የንብረት መመለሻ ደረሰኝ፣ የንብረት ወጭ ደረሰኝ፣ የእለት ገንዘብ መሰብሰብያ ገቢ ደረሰኝ፣ ቢን ካርድ፣ ስቶክ ካርድ የዕጣ ሰርተፊኬት፣ ቢዝነስ ካርድ፣ የሂሳብ ማስተካከያ ደረሰኝ፣ የአጅ በእጅ ገንዘብ መቀበያ ፋክቱር፣ ሎት 3 ካባዛባቸው ዘር ብዜት ማህበራት ማለትም ድል በትግል፣እድገት መሰረት፣ ሰላም ለሁሉም፣ እድገት በር፣ ፈንድቃ፣ ጉደር፣ ሰከላ ፣መጋቢው፣ ሰባዳር ምርጥ ዘር ስንዴ እና በቆሎ ዘር ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም ተጫራቾች 145 ኩ/ል የመጫን አቅም ያለው ወይም ከዚያ በላይ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም ሎት 4 EGA 500 0.40/90cm bule ቆርቆሮ ከሎት 1-4 በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በጨረታው ተጫራቾች በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ለጨረታው የቀረበውን ዝርዝር መረጃ በጨረታው ሰነድ ላይ ይገኛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በጥሬ ገንዝብ ወይም በሚጫረቱበት ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ያለበለዚያ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ኦርጅናል ከሆነ ደግሞ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረብያ ሰነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመበት እና የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት መሆኑን በማረጋገጥ እና በፖስታ ላይ 3 ቦታ ማህተም በማድረግ በማሸግ ዩኒየኑ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ትራንስፖርት ለማጓጓዝ ለተከታታይ 7 ከቀን ከህዳር 22/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2018 ዓ.ም እና ለህትመት ለጽህፈት መሳሪያ እና ለቆርቆሮ ለተከታታይ 10ቀናት ህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 1/2018 ዓ/ም 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለትራንስፖርት ለማጓጓዝ ህዳር 28/2018 ዓ.ም 4፡00 ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለህትመት፣ ለጽፈት መሳሪያ እና ለቆርቆሮ ታህሳስ 1/2018 ዓ/ም 4፡30 ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጎልም፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ጨረታው በተከፈተ አሸናፊነቱ በተገለፀበት በዕለቱ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈበት ዋጋ 10 በመቶ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዩኒዩኑ ለሚከፍለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ምርቱን ዩኒዩኑ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ያሉትን ለማሳያ ናሙና ከእያንዳንዱ ምርት ማሳያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ ማሟላት አለባቸው፡፡
- ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒዩኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 874 58 89 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡ አድራሻ ቡሬ ከተማ ከዳሞት ዩኒዩን 600 ሜትር ወረድ ብሎ ወይም ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ነው፡፡
የዕድገት በአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒዩን ኃ.የተ

