በአብክመ በምስ/ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ አስ/ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የጽዳት እቃዎች ፣ሎት2. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት3. ህትመት ፣ሎት4. የህንፃና ተገጣጣሚዎች እድሳት የሚውል ግብዓት ፣ሎት5. ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጫረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ታትሞ የሚቆይ ሲሆን፤ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት አስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡15 ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
- የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 ብር 50 /ሀምሳ ብር/ የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝርመግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 66 10 002 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች 20በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው
- የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
የሞጣ ከተማ አስ/ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት

