በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
53

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደባይ ጥላት ግን ወረዳ የቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ቤት በ2018 የበጀት አመት በከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈልጋል፡፡ በመሆነም ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል ወይም ጠጠር የሚመረትበትን ቦታ ማዘጋጃ ቤቱ የሚያሳይ ሲሆን በጥራት የሚሰራ ሆኖ ከተጫራቾች መካከል አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ የማሽን ፈቃድ ያላቸው አካላት ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በወጣው የሥራ ዝርዝር መሰረት ሁሉንም ወጭ የሚችል ማለትም ለመንገድ ሚያስፈልገውን ነዳጅ የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ (ሎቬድ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ሁኖ የጠቅላላ ገቢ ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ ያላነሰ እና ከ2 በመቶ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን ተወስኖ በጨረታ ጥሪዉ እና ሰነድ ዉስጥ መገለጽ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ የሆነ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቁይ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የግዥ ጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸዉን ፊርቸውን ሙሉ አድራሻቸውን የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ፓስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የማሽን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ የሚቆይበት በ21 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልተገኙበት ቢሮ ቁጥር 07 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ የስራ በ22 ተኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ባወጡት መስሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. በዉድድሩ የተገኘዉ ዋጋ ሳይቀር መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  16. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ሎት ሞልቶ ካቀረበ ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገድ የሚያስፈልጉ ማንኛዉንም ማቴሪያል ወይም ቁሳቀስ ትራንስፖርት ቦታው ድረስ እራሱ የሚያጓጉዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
  19. ተጫራቾች የጨረታውን መጠን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  20. ሥርዝ ድልዝ ካለው ልዩ ፊሪማ መቀመጥ አለበት ልዩ ፊርማ ከሌለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  21. አድራሻችን በምሥራቅ ጎጃም ዞን/ደ/ጥ/ግ/ወ/ቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአዲስ አበባ 284 ኪ.ሜ ከባህር ዳር 324 ኪ.ሜ ከደብረ ማርቆስ – ቁይ 60 ኪ.ሜ ላይ ተገኛለች፡፡
  22. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 62 78 65 91 /09 20 50 69 44 መደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ (ሎቬድ) ተጫራች የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚቻለዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአቢሲንያ ባንክ፣ ቡና ባንክ እና ዓባይ ባንክ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ቀይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here