የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 የኤሌትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 100,000 /ከአንድ መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጫማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር በወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በሁለት በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በጥንቃቄ ተሞልቶ በሻ/መ/ደ/ሆስፒታል በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም በ11፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸግና ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በሻ/የመ/ደ/ሆስፒታል 3:00 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት ማምጣትና በጥራት ኮሚቴ አስገምግሞ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ የሚለየው በድምር ነው፡፡
የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

