በአማራ ብሔረዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ አስተዳደር ዞን የሚገኘው የአድማስ ሁለ/የገበ/ የኀ/ሥ/ ማኀበራት ዩኒዬን ኃ.የተ የድርጅቱን የውስጥ አሰራር በዘመናዊ አሰራር ላማዘመን የወጣ ጨረታ ሎት.1 ዩኒዮኑ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ሶፍት ዌር ማበልፀግ (ERP) System (የዋና ቢሮ እና የፋብሪካ አጠቃላይ የፋይናንስ ስራ ፣ የፋብሪካ ጥሬ ዕቃ እና ያለቀለት ምርት ፣ የሰብል ግብይት ፣ የግብርና ግብአት ፣ የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት የኢንቨንተሪ ሲስተም (inventory system)፣ የሰው ሀይል አሻራ Biometric and finger print software development መስራት፣ ሎት2. የመኪኖች ጂፒኤስ እና ሶፍትዌር ግዥ እና Installation ስራ ለማሰራት ከተጫራቾች በቀረበው ሰነድ አወዳድሮ በቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ፣ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት በኢትዮጵያ ብር 50 (ሃምሳ ብር ) ብቻ ከፍሎ የዩንዬኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር የጨረታ ዝርዝር ሠነዱን በመግዛት የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ የድርጅቱን ስም፣ማኀተም እና በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ በተዘረዘረው መሠረት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ያሳውቀ፡፡
- የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋችሁን በሠንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር ሁኔታ መሠረት መሙላት አለባችሁ፡፡
- የጨረታ ዋጋው ከመገለጹ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረገጋጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባችሁ፡፡
- ከዚህ በፊት በዘርፉ ከሰሩበት መ/ቤት የመልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ 3 እና ከዛ በለይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በሎትም በጥቅልም መወዳዳር ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ወይም ከሕዳር 29/2018 እስከ 8/04/2018 ዓ.ም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡የጨረታው መክፈቻ የህዝብ በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዢ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው እንደታወቀም አሸናፊው የአሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 ቀን ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ማስከበሪያው ሁለት በመቶ ይወረስበታል፡፡
- ከጨረታው ጋር በተያየዘ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ተገዥ የሚሆኑ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ 058 227 16 81/09 98 0 127 00 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአድማስ ሁለ/የገበ/ የኀ/ሥ/ ማኀበራት ዩኒዬን ኃ.የተ

