የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት3. ህትመት፣ ሎት4. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት5. ፈርኒቸር፣ ሎት6. ሌሎች ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- በሎት ከጠቅላላ ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ በመቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደረጋል፤ ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በ50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠዉ ወይም የሚለዩት በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ነዉ፡፡
- አሽናፊው ድርጅት ያአሸነፈዉን እቃ በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፍቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 03 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ጐን/ አስ/ ዞን /ከፍ/ ፍ/ቤት

