ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በባህር ዳር ከተማ አስ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ፤የጽህፈት መሳሪያ፤የፕሪንተር ቀለም እና የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር  የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው ፡፡
  3. ጨረታው ዋጋው ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመግዛት ባ/ዳር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ከግዥ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 46 መውሰድ ይቻላል::
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ለመኪና ጎማ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ) ብር፣ ለጽህፈት መሳሪያ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) ፣ ለፕሪንተር ቀለም ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) እና ለጽዳት እቃ ብር 40,000 (አርባ ሸህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ባህር ዳር ከተማ ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ግዥው/አገልግሎቱ/ ከብር መጠን 20,000 (ሀያ ሸህ) ብር በላይ ከሆነ ቫት የምንቆርጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ዝቅተኛ የሞላ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው በ16ተኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 220 93 73 በመደወል ወይም በአካል ባህር ዳር ከተማ ገንዘብ መምሪያ በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here