የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም ፡- ሎት 1. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችና መገልገያዎች፣ ሎት 2. የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የኮምፒውተር መሳሪያዎችና ተጓዳኝ እቃዎች እንዲሁም ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኜት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ከት/ቤቱ ገ/ያዥ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ (በሲፒኦ) ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነበር፣ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ህዳር 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ ሥርዝ መኖር የለበትም፡፡ ነገር ግን ሥርዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሎት የጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ምርቱን /እቃውን/ በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

