በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከወግዲ መካነ ሰላም ጠጠር መንገድ ቆረጣና ጥገና ሥራ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ /GC/ እና የመንገድ ሥራ ተቋራጭ /RC/ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የቆረጣና የጥገና ሥራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ተሳታፊዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ታዋቂ የልማት ድርጅቶች በተመሳሳይ ሥራ የሰሩበትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም አብረው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) የባንክ ጋራንቲ ዋና (ኦርጅናል) ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ ተቀባይነትም የለውም፡፡
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 1500 /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ወልዲያ ከተማ በሚገኘው ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን 4:00 ላይ ታሽጎ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ሰዓት ማለትም ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጠራና ግልጽ የሆነ የድርጅታቸውን ቴክኒካል ዶክመንት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ተቋቁሞ መስራት የሚችሉ ብቃት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸንፈው ውል ከወሰዱ በኋላ ያለምንም ቅድመ ክፍያ መስራት ስለመቻላቸው የሚገልጽ ዶክመንት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ክፍያን በተመለከተ የተሰራው ሥራ በአማካሪዎች በጸደቀው መሰረት የሚከፈል ይሆናል፡፡
- በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ብቻ መሙላት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

