ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
188

የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ለኮሌጃችን አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት አመት ለሚገዙ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4 ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣ ሎት 5 የልብስ ስፌት እቃዎች እና ሎት 6 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኃል፡፡

  1. ማንኛውም ህጋዊ የሆኑና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪው መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 05 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስታና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በድጎ-ፅዮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ከረፋዱ 3፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ኮሌጁ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ከላይ በሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ኮሌጁ የእቃዎችን ናሙና በሚፈልግበት ጊዜ እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. በሌላ በኩል አሸናፊው ድርጀት እቃዎችን በሙሉ በኮሌጁ ውስጥ ሊያቀርቡና በጥራት ኮሚቴው ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
  15. ኮሌጁ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 64 56 02 95 /09 13 23 29 21 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የድጎ-ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here