የጨረታ ቁጥር፡-001/2018
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ እና በተለያዮ ፕሮግራም በጀት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክ) ላፕቶፕ ፣ዴስክ ቶፕ ፣ፕሪንተር ፣AC ወዘተ ፣ ሎት2. የተሸከርካሪ መለዋወጫና ታፒሰሪ (ዲኮር)፣ ሎት3. ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ ፣ ሎት4. የቢሮ መገልገያ እቃዎች (ፈርኒቸር)፣ ሎት5. የተሸከርካሪ መለዋወጫና fast moving እቃዎች ፣ሎት6. ዘይትና ቅባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን የንግድ ዘርፉ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሎት.1 ብር 40,000.00፣ ለሎት2. ለተዘረዘሩት ብር 20,000 ፣ለሎት3 ፣4 ፣5 እና ለሎት 6 ብር 5000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላለሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 87 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ወይም ቀበሌ 07 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ

