በአፈ/ከሳሽ ዳዉድ ሙሀቤ እና በአፈ/ተከሳሽ ጌታቸዉ ጥላሁን መካከል ስላለዉ የገንዘብ ክስ ክርከር ጉዳይ አፈ/ ተከሳሽ በጌታቸዉ ጥላሁን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በፈንድቃ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኝ አዋሳኙም በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ 788፣ በሰሜን 796 እንዲሁም በደቡብ 798 በሚያዋስነዉ መካከል የሚገኝ ቤት መነሻ ዋጋ ብር 1,684,000 /አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰማኒያ አራት ሺህ ብር/ የሸጣል፡፡ ስለሆነም የጨረታ ማስታወቂያው ከታህሳስ 03/2018 እስከ ጥር 03/2018 ዓ/ም ለ30 ቀን በጋዜጣ እንዲውል በማድረግ ጥር 04/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋዉን 1/4ኛዉን ብር በማስያዝ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍ/ፍ/ቤት

