በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለተቋም ሥራ የሚውል እስቴሽነሪ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግብር የከፈሉበት ክሊራስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታው በሎት ድምር ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በሲፒኦ በባንክ በክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ስም ያስይዛሉ፡፡
- ጨረታው ከ1-5 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫረቾች (ህጋዊ ወኪሎቻው) በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 12 በ15ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡ የአንድ ሰነድ ዋጋ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ነው፡፡
- የእስቴሽነሪው (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቹን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም በመግለጽ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት ባዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይቆያል፡፡ አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በ5 ተከታታይ ይቀናት ክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ 09 18 71 44 11 መደወል ይችላሉ፡፡
የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

