ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
95

የቢቡኝ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት አመት ለሚገዙ እቃዎች ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት 2 አላቂ የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 6 ፈርኒቸር የህንፃ መሳሪያ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪው መሥሪያ ቤት፣ የተጫራቾችን ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ለክፍያና ማጠቃለያ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማሰያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢቡኝ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ባይገኙም በግዥ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም 3፡00 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ከላይ በሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ መ/ቤቱ የእቃዎችን ናሙና በሚፈልግ ጊዜ እንዲያቀርቡ የሚጠየቅ መሆኑን እየገለፅን በሌላ በኩል አሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) እቃዎችን ሙሉ በሙሉ ከቦታው ድረስ በማቅረብ በጥራት ኮሚቴው ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ በጨረታው 20 በመቶ የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 05 11 /09 28 51 63 78 /09 21 88 12 09 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here