በሰሜን ጎንደር ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ የመካነ ብርሃን ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለማሰልጠኛ እና ለቢሮ ለጽህፈት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የአይሲቲ ዕቃ፣ ሎት 3 ኮንስትራክሽን እንዲሁም ሎት 4 የፈርኒቸር ሜኪንግ (ያልተዘጋጁ ዕቃዎች) የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የግዥ መጠናቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ውድድሮች የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የታክስ ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሪላነስ (የምስክር ወረቀት ) ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልጽ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሥርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የድርጅታችሁን ህጋዊ ማህተም ከፖስታው እና ከጨረታ ሰነድ ላይ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር በሎት ምድብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል እና በመውሰድ በጥንቃቄ በመሙላት መ/ብ/ቴ/ሙ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ደግሞ የከፈሉበትን በመ/ቤቱን የመሂ 1 ደረሰኝ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር የለለ (ሲፒኦ) ወይም የመሂ 1 ደረሰኝ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚውል ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሸጎ በ4፡00 ላይ መ/ብ/ቴ/ሙ/ኮሌጅ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ኮሌጁ ጨረታውን ከመከፈት የሚያግደው ሁኔታ አይኖርም፡፡
- የጨረታ የማሸጊያ እና የመከፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን የማይውል ከሆነ የማሸጊያ እና የመክፈቻ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት የጫኝ፣ የአውራጅና የትራንስፖርት ወጭን የሚሸፍን ሲሆን በተጨማሪም የግዥ ውል የሚወስደው ጃናሞራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መ/ብርሃን ላይ ሆኖ ማቴሪያሉንም ኮሌጁ ድረስ የሚስረከብ ይሆናል፡፡
- የእቃዎች ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 22 71 26 48 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመካነ ብርሃን ቴከኒና ሙያ ኮሌጁ

