ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
57

በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የተንታ ወረዳ ፍ/ቤት የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ ህትመት፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣  ሎት 6 ተሰርተዉ የሚሸጡ ፈርኒቸር ወይም (ቋሚ) እቃዎች እንዲሁም ሎት 7 የሚሰሩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት (ለማሰራት) ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግብር ክፍያ መለያ ወይም (ቲን) ያላችሁን ማስረጃዎቹን ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነትን የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ከፍለዉ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች ያሸነፈዉን ዋጋ በተናጠልም ሆነ በጥቅል ዋጋ ከብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሶስት በመቶ የሚከፍል ይሆናል ፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ዉስጥ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  13. የጨረታዉ አሸናፊ መሆን የሚቻለዉ የተጫረቱበት ዘርፍ በሎት ዝቅተኛ ዋጋ የሰጡ መሆኑን ታዉቆ ለሞሉት ጥቅል እቃዎች ዋጋ ማስያዝ ሲችሉ ነው ፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉትን አቅርቦት ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ን/ክፍል ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀን ዉል መፈጸምና የዉሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡
  16. ሌሎች ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሁነዉ የእቃዉን ብዛት እስከ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይሆናል፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  19. አቅራቢዉ በዉሉ መሰረት በጊዜዉ አጠናቆ ባያቀርብ በዉሉ የተመለከተዉን ገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ አንድ በመቶ መቀጫ እንደሚከፍል ማወቅ አለበት፡፡
  20. ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም፡፡
  21. ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 02 61 ወይም 09 06 91 64 97 በመደወል መረጃ ማገኘት ይችላሉ፡፡

የተንታ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here