ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
165

የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2018

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ የሚያሰራውን Shade Bulding Cobblestone Pavements, Berige Bulding, Dranage /Dich/ Bulding ሥራዎች ሽድ ግንባታ  ሎት 1 በፓኬጅ ቁጥር AMH/INJBARACIP/CW04/25/2026 በGC እና BC ኮብል እስቶን ማንጠፍ ሎት 1 AMH/INJEBARA/CIP/CW 01/25/2026 በGC እና RC  ድልድይ ሎት 1 ሎት 2 AMH/INJEBARA/CIP/CW03 /25/2026 በGC እና RC ዲች ግንባታ AMH/INJEBARA/CIP/CW/06/25/20268 GC,RC,  በደረጃ 7 እና በላይ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዘው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው  ሲሞላ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ህዳር 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም 3፡30 ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 1 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን በእን/ከ/አስ/ከተማ/መ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሺድ ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለድልድይ ሎት 1 ብር 346,000 /ሶስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ብር/ ለሎት 2 ብር 364,000 /ሶስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ብር/ ለኮበል ንጣፍ ለሎት 1 ብር 116,000 /አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ ብር/ ለዲች ግንባታ ለሎት 1 ብር 146,000/አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ብር/ ለሎት 2 ብር 46,000 /አርባ ስድስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ እና በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ጥቃቅን ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እና ከተደራጁ 5 አመት ያልሞላቸው ለመሆን ከአደራጅ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ የተጋነነ ዋጋ ዝቅታኛ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ያስይዛል፡፡ ውል በሚይዝበት ወቅት ማስያዝ ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ጥቃቅን ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
  9. አሸናፊ ድርጅት የሚሰራቸውን ከላይ የተዘረዘሩትን ፕሮጀክቶች (ሥራዎች) ማንኛውንም ማቴሪያሎች ወጭ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በተሻሻለው መመሪያዎች መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  12. የውል ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  13. ለተጨማሪ መረጃ የእን/ከ/አስ/ከተማ/መ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋይ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 00 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here