ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም ሎት 6 የቢሮ መገልገያ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 29/2018 እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 31 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የድምር ሎት 1 ብር 40,00፣ ሎት 2 ብር 8,000፣ ሎት 3 ብር 5,000፣ ሎት 4 ብር 7,500፣ ሎት 5 ብር 60,000 እና ሎት 6 ብር4,500 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገንዘብ ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 14/2010 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውበቱን ጠቅላላ ድምር ውጤቱ ያያል፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን  ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡

የደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here