የሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ቀለብና የምግብ ማብሰያ እንጨት፣ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር ማምረቻ ዕቃ፣ የግንባታ ማቴሪያሎች እና የጽዳት እቃዎች አጠቃላይ ለመ/ቤታችን ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማቴሪያሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 01. ሰርገኛ ጤፍ፣ ደብር ማሽላ፣ ሎት 02. ምጥን በርበሬ ባቄላ ክክ፣ ምጥን ሽሮ፣ የተፈጨ ጎመን ዘር እና ያልተፈጨ ጎመን ዘር፣ ሎት 03. ፊኖ ዱቄት፣ ሎት 04 የሚረጋው ዘይት፣ ሎት 05 የማገዶ እንጨት፣ሎት 06 የጽህፈት መሳረያ፣ ሎት 07. የጽዳት ዕቃ ሎት 08. የደንብ ልብስ፣ ሎት 09. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 10. የፈርኒቸር ማምረቻ እቃዎች እንዲሁም ሎት 11. የግንባታ ማቴሪያሎች ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- የታደሰ የዘመኑ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ሰርፊተኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረ (ሲፒኦ) ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም ያስያዙት (ሲፒኦ) ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ በብር 30 (ሰላሳ ብር) ደባርቅ ማረሚያ ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡ ጨረታው ከታህሳስ 6/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም ከደባርቅ ማረ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችለሉ፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16 ተኛው ቀን 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቢሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ማንኛውንም መረጃ ፎቶ ኮፒ አባሪ በማድረግ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚለየው በሎት ዋጋ ይሆናል ተጫራቾችም ሁሉንም ዕቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች እቃውን የሚያስረክበው ሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተወዳዳሪ ለሚወዳደርበት ጨረታ በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ 10 በመቶ ነጣጥሎ ማቅረብ አለበት፡፡
- ሎት 05፣06፣09፣10 እና 11 ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ ነጋዴዎች የሚያሸነፉበት ዋጋ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ይከፍላሉ፡፡
- የስሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች ውል መውሰድ የሚችል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ 20 በመቶ የሚጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 117 04 19 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ

