በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለማስተማሪያ ጥሬ ዕቃዎችን እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው የምትሳተፉ ድርጅቶች በቀረበው የጨረታ ዝርዝር በንግድ ፈቃዱ መሰረት በሎት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪዎች /እስቴሽነሪ/ መደብር፣ ሎት 2. የህንፃ /ኤሌክትሪክ መሳሪዎች መደብር፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ መደብር፣ ሎት 4. የጨርቃ ጨርቅ መሸጫ መደብር፣ ሎት 5. የመኪና መለዋወጫ ድርጅት እና ሎት 6. ህትመት ድርጅት የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ተወዳዳሪዎች
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢንድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከ2 በመቶ ያልበለጠ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መቆያ ጊዜ ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16 ተኛው ቀን ማለትም ታህሳስ 21 /2018 ዓ.ም ሲሆን ከቀኑ 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በዚሁ እለት ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም በ4፡30 ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በቀረበው የመጫረቻ ሰነድ መሰረት ሙሉ በሙሉ ዋጋ ካልሞሉ በጨረታው አይወዳደሩም፡፡
- ስለጨረው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መረዳት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ እቃውን ከኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት (ግለሰብ) ማሸነፉ በተገለፀ በአምስት ቀን ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀ በ5 ቀን ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡
- ከላይ ከተገለፀው ሃሳብ ውጭ ያልተገለፀ ሀሳብ ካለ በግዥ መመርያው የምንገዛ ይሆናል ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኮሌጁ ግ/ፋ/ን /አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

