ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

ቁጥር 01/18

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
  4. የሚጫረቱበት ጨረታ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 45,000 እና ሎት 2. ብር 24,000  በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ወይም (በሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋጋ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. የእቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳብን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመርሳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በ16ኛው ቀን ታህሳስ 21/2018 ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ሥርዝ ድልዝ እና ፍሉድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ከጨረታ ዉጭ ያስደርጋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ጸንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀን የጸና ይሆናል፡፡
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም 09 13 28 23 42 /09 35 21 25 15 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here