በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ እታለም ምስጋኔ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ፍቃዱ አምባዬ መካከል ባለዉ የባል እና ሚስት ክርክር በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ቀበሌ 01 ልዩ ቦታዉ ሀሙሲት አዋሳኙም በምሥራቅ የወ/ሮ መሬም አብደላ ቤት እና ቦታ፣ በምዕራብ የሺህ ሰይድ ሁሴን ቤት እና ቦታ፣ በደቡብ መንገድ እንዲሁም በሰሜን መንገድ በሚያዋስኑት 432.25 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ ቤት እና ቦታ መነሻ ዋጋ 3,911,118.22 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ሺህ አንድ መቶ አስራ ስምንት ብር ከሃያ ሁለት ሳንቲም) በማድረግ በጨረታ ተጫርቶ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡ ስለሆነም ጨረታዉን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አንድ ወር የሚቆይ መሆኑን እና ጨረታዉ የሚከፈትበት ቦታ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
የመቄት ወረዳ ፍርድ ቤት

