የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
143

የደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማት ማኔጅመንት እና ባንክ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት የቦታ ስፋታቸዉ እያንዳንዳቸዉ 500 ካ.ሜ 03 (ሶስት) ለድርጅት (ለንግድ) የሚውሉ ቦታዎች በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም ሰዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከታህሳስ 06/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና ለእያዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከታህሳስ 06/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ቦታዉን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸዉ መርሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታዉ የሚዘጋዉ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
  5. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡
  6. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በጋዜጣ እና በአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ዌብ ሳይት ማየት እንዲሁም በደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በሳይት ፕላን ላይ በተገለፀዉ እና በከተማዉ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት ደረጃዉን የጠበቀ ግንባታ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 47 58 18 /09 31 63 37 72 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡

የደጋን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here