የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተያዘው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚገዛቸው የተለያዩ እቃዎች እና የሚያሰራቸው ስራዎች ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ ፣ሎት2. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት3.የደንብ ልብስ ፣ ሎት4. ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት5. የህንፃ መሳሪያ ፣ሎት6. የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት7. ፈርኒቸር ፣ሎት8. ህትመት፣ ሎት9. ጄኔሬተር ሰርቪስ ማድረግ፣ ሎት10. ጭነት አገልግሎት (ኦክስጅን ስሊንደር እና መድሃኒት ከባ/ዳር ጭኖ ማምጣት)፣ ሎት11. ግንባታ ስራ ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ ፣ የካርድ ክፍል ማስፋፊያ ፣ የበር ታፔላ ስራ ሙሉ እቃዎችን ሆስፒታሉ ችሎ የሚያቀርብ ሲሆን ተጫራቾች የእጅ ዋጋ ብቻ አስበው የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ ሎት12. የኦክስጅን ስሊንደር ግዥ እና ሎት13. ኦክስጅን አስሞልቶ ጭኖ ማምጣት፤ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን ) ያላቸዉ፡፡
- ግዥው ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር)ዘ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- በግንባታ ስራ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- በግንባታ ስራ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች እና የሚሰሩ ስራዎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃዎች ግዥ፣ አገልግሎት፣ ሰርቪስ (ጥገና ስራ) እና ግንባታ ስራ ብር ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በማሸግ ማስያዝ እና በጥቃቅን መ/ቤት የተደራጁ ከሆኑ ካደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ በአድራሻችን በመፃፍ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታዎች በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቡሬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጨራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሶስት በመቶ ይቀነሳል፡፡
- ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅበቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊ ተለይቶ ውል ከተያዘ በኋላ ከግንባታ እና ከሰርቪስ (ጥገና ስራ) ውጪ በራሱ ወጪ እስከ ቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን በመምረጥ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ግንባታ ስራ ላይ ሙሉ ማቴሪያሉን ሆስፒታሉ ችሎ የሚያቀርብ ሲሆን ተጫራቾች የእጅ ዋጋ ብቻ አስበው በመሙላት እና መወዳደር የሚችሉ መሆን እናሳስባለን፡፡
ቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

