ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በመደበኛና በውስጥ ገቢ በጀት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት ምድብ 1. የጽህፈት መሳሪያ ንዑስ ምድብ 1.1 ቋሚ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ ሎት ምድብ 2. የህንፃ መሳሪያ እቃዎች ንዑስ ምድብ 2.1 የህንፃ መሳሪያ (የቴክኖሎጅ)፣ ንዑስ ምድብ 2.2 የህንጻ መሳሪያ ጥገና እቃዎች፣ ሎት ምድብ 3. የኤሌክትሪክ (ኤሌክትሮኒክስ) ፣ ሎት ምድብ 4. የጋርመንት ልብስና ክሮች ንዑስ ምድብ 4.1 የጋርመንት (የቴክኖሎጅ እቃዎች) ፣ ሎት ምድብ 5. የግብርና እቃዎች፣ ሎት ምድብ 6. የአውቶ ሞቴቭ እና የመኪና እቃዎች፣ ሎት ምድብ 7. ኮምፒውተር እና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ ሎት ምድብ 8.የጽዳት እቃዎች፣ ሎት ምድብ 9. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት ምድብ 10. ህትመት፣ ሎት ምድብ 11. ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ንዑስ ምድብ 11.1 ሸሚዝ ንዑስ ምድብ 11.2 ጫማ ግዥ ይፈፅማል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትችሉት ከላይ ከሎት ምድብ 1 እስከ 11 ሎቶች እና ንዑስ ምድብ ላሉት በመስኩ የተሰማራችሁ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ሆኖ ማንኛውንም ውጭ በተጫራቾች በኩል የሚሸፈን ይሆናል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ግምታቸው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆኑ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ውድድሩ በሎት በመሆኑ ተጫራች የእያንዳንዱን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የዋጋ ዝርዝር ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 6/2018 እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ምድብ የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከታህሳስ 06/2018 እስከ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ድረስ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከታህሳስ 06/2018 እስከ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ድረስ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በዚሁ ቀን ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ የሚገባቸው ካሉ የሚያቀርቡ ሆኖ ጥራቱ በባለሙያ እየተረጋገጠ ለምሳሌ የኮምፕተር ወርቀት እንድሁም ሌሎች ማቴሪያሎች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖራባቸዋል፡፡
  10. ሁሉንም ዕቃዎች ኦርጅናል ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለምሳሌ የፕሪንተር ቀለም እና ሌሎችም እቃዎች ኦርጅናል ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
  11. በጨረታ ሰነድ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ውል ከመውሰድ በፊት 20 በመቶ በጀቱ እየተጣጣመ መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል ሲሆን በጀቱ እየታየ የሚሰርዝ ሎት ይኖራል፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት በ10 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በራሳቸው ወጭ ዕቃውን በማጓጓዝ ወልዲያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ሁኖ ንዑስም በየራሳቸው ንዑስ ድምር አሸናፊ ይለያል፡፡
  13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 331 04 19 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወልድያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here