አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለስራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ በማህበሩ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት የሚገኙ የተለያዩ ያገለገለ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ (ድርጅት) መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሠነዱ ላይ በማየት በማህበሩ ዋናው መ/ቤት እና አዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት በአካል ተሽከርካሪዎችን በማየት ዋጋውን በዋጋ መሙውያው ቅጽ መሠረት ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላትና በፓስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G- 03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የተሽከርካሪ ዋጋ ከመነሻ ዋጋ ማነስ የለበትም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ዋጋ የሞሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከማህበሩ ጋር አስፈላጊውን የውል ስምምነት በመፈፀም ውል ከያዙበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አሰር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት መረጃ ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)

