የአዴት ሆስፒታል የግዥ /ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የፅህፈት መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንጋብዛለን፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የክፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የፅህፈት መሳሪያዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 40 (አርባ ብር) ብቻ በመክፈል አዴት ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ የስ/ ሂደት ከገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢን ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጫራታ ሃሳቡን በአንድ ፖስታ ዋና ወይም ኦርጅናል በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዴት ሆስፒታል በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በቀን ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን ማለትም የፅህፈት መሳሪያዎችን አዴት ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ድርጅት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 83 82 757 ደውለው ማግኘት ይችላሉ ወይም ቢሮ ቁጥር 08 በአካል ቀርበው ማናገር ይችላሉ፡፡
የአዴት ሆስፒታል

