ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ የአካባቢ መልሶ ማገገም እና ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም ፡ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ለፕሮግራሙ አገልግሎት የሚውል የልማት መሳሪያ (የጋቢዮን) ሳጥን፤ አዷማ፤ አካፋ፤ መዶሻ; መናኪሎ እና የውሃ እቃዎችን  በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር  ትችላላችሁ፡፡

  1. ዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት  ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በባህር ዳር  ዋና መ/ቤት ድረስ በመቅረብ  የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡ አቅራቢዎች እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ናሙና (ሳምፕል) ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
  5. አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ የድርጅታችን ስም በመግለፅ በኢቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የእቃዎቹን ዋጋ ሞልተው አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፤ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  8. የተሰረዘ፣ የተደለዘ፣ የተፋፋቀ ወይም በግልፅ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. አሸናፊዎች እቃዎቹን እስከ ዋና መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  አድራሻ፡-ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 13 ትምህርት ቢሮ ጀርባ ስልክ ቁጥር 058 220 5 160

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here