በአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 ኮምፒተርና ተዛማጅ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6 ተገጣጣሚ የቢሮ እቃዎችን፣ ሎት 7 የህትመት ውጤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ገቢ ማድረግ ደረሰኙን ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የእቃ ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ከደ/ማ/ከ/አስ/ፖ/መምሪያ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ከንቲባ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በማሸግ የተጫራቹን ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ በመፃፍ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ መልሶ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ዝግ ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ዉድድር የሚካሄደዉ በሎት (ጥቅል) ዋጋ ሲሆን ለሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት አለበት፣ ካልተሞላ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል በመያዝ አገልግሎቱን መስጠት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ከእያንዳንዱ እቃ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- አሸናፊው በራሱ ትራንስፖርት የደ/ማ/ከ/አስ/ፖሊስ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጨረታ ማስታዎቂያውና በተጫታቾች መመሪያ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ የደ/ማ/ከ/አስ/ፖሊስ መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 49 48 11 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ

