የባሕር ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተርና ላፕቶፕ እቃዎች፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያዎች፣ ሎት 5. አመታዊ የኮምፒወተር ጥገና ሰርቪስ እንዲሁም ሎት 6. የተለያዩ ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ሊሆኑ ይገባል ሌሎች ያልተጠቀሱ ቢኖሩ በመንግስት የግዥ መመሪያ በሚፈቅደው ተፈጻሚነት ይኖርዋል፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዘጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ማሸነፋ ከተገለፀበት ከ5ኛው ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አሽናፋው የሚለየው በጥቅል ሎት ድምር ነው፡፡
- ተጫሪቾች ለሚጠየቁት የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 058 226 54 93 ወይም እንስሳት ላብራቶሪ በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ላብራቶሪ

