ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
62

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የደምቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ ሎት2. የጽዳት እቃዎች ፣ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የሆስፒታሉ የውስጥ ለውስጥ ግንባታ እድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች  የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ሰርት ፍኬት ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 ያሉት በሙሉ የሚያሟሉ መሆን አለባቸው ማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ለጨረታው ማሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ሆስፒታሉ ጨረታውን የመክፈት ሥልጣን አለው፡፡
  5. ሰነዱን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደንቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋይናስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ሰዓት ከ13/4/2018 ዓ.ም  እስከ 1/5/2018 የጨረታ ሰነዱን ሳጥኑ እስኪታሸግ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00  የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት  ሲመጡ ናሙና የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች ማየት ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው  በሎት ወይም በነጠላ ዝቅተኛ  ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድረጅታቸውን ማህተም፤ ፊርማ ከሁሉም የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም፤ ሆኖም ግን ስርዝ ካለው ፊት ለፊት ፓራፍ ላይ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ዋስታና (ቢድቦንድ) የጠቅላላውን ዋጋ1 በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡
  12.  ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቀጥር 09 34 39 59 29/ 09 87 87 41 81 ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

ማሣሰቢያ፡-ጨረታው ከዚህ በፊት  የአፈፃፀም ችግር ያለባቸውን  አይመለከትም ፡፡

የደምቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here