ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
68

የመተማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን አድራሻ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደ ውሃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 ስልክ ቁጥር 09 06 42 42 30 የሚመጣውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ወርሃዊ ኮታ 1,562 ኩንታል ስኳር ውስጥ የኢትዮጵያ ስኳር እንዱስትሪ ጉሩፕ እንደሚመድብልን የኩንታሉ መጠን ከተለያዪ የስኳር ፋብሪካዎች ማለትም መትሃራ ስኳር ፋብሪካ፣ ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ አዲስ አበባ ስኳር መጋዘን ላይ ለማምጣት እንዲሁም አዲስ አበባ፣ ባሕር ዳር፣ ቡሬ እና ጎንደር የምግብ ዘይት፣ ፊኖ ዱቄት፣ የእንሰሳት መድሃኒትና ፀረ አረም እና የተለያዪ ሸቀጣሸቀጦችን ለማስመጣት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከገንዳ ውሃ ከተማ ድረስ ማስመጣት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ የማስገቢያ ቀንና ስዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲፒኦ ከታወቀ ባንክ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ራሳቸው ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 12፡00 እና ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡30 ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. የመጫረቻ ሰነድ ማስገቢያ ቦታ መተማ/ሁለ/የገ/ህ/ሥ/ማ/ዪኒየን ቢሮ ቀርቦ የጨረታ ሳጥን በተዘጋጀበት ቦታ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀርቦ የሞላበትን የገንዘብ መጠን 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  12. ጨረታውን ያሸነፈ ትራንስፖርተር ለ6 ወር ለማጓጓዝ ውል የሚገባ መሆን አለበት፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል /እሁድ/ ቢሆን በቀጣይ የሥራ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  14. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ ስልክ 09 06 42 42 30 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  16. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመተማ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here