በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 አነስተኛ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6 ህትመት፣ ሎት 7 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ሎት 8 የቢሮ ጥገና እንዲሁም ሎት 9 የመስተንግዶ ሻይ ቡና የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱት የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ማለትም ቲን ነምበር፣ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት ለሚያስፈልጋቸው ግዥዎች የቫት ሰርተፊኬት እና በውክልና የሚሰሩ ከሆነ የውክልና ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ከፖስታው ውጭ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ካስፈለገ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በመስሪያ ቤቱ አካውንት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከደጥ ግን ወረዳ ፍርድ ቤት በብር 100 (አዘንድ መቶ ብር) ይሸጣል፡፡ እንዲሁም የእቃው ዋጋ ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በመግለጽ እና በታሸገ ፖስታ እና ማህትም በማሳረፍ ደ/ጥ/ግን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ በሎት የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው አሸናፊ ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ እቃውን ገቢ በሚያደርግበት ወቅት ጥራቱን በባለሙያ ተረጋግጦና የታሸጉ እቃዎችን ተፈተውና ታይተው የምንረከብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ሲሆን በዚሁ ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታ በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታውን መክፈት የሚያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ደ/ጥ/ግን/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 257 02 81 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ካቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ እንዲታወቅ፡፡
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እስከ 20 በመቶ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ እንደሚችል ይታወቅ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ሥርዝ ድልዝ ካለበት መፈረም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደ/ጥ/ግን/ወ/ፍ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 257 01 19 /058 257 02 81 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፍርድ ቤት

