የጨረታ ቁጥር 03/2018
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው በውጭ ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ፡፡
- የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍለው የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በክልል 3 ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በድርጅቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለዉ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን ታክሱን ጨምሮ በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ያስገባ፣ ዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማሲያዣን በፋይናንሽያን ፖስታ በማሸግ መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ2 ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 5 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 033 551 02 72 ወይም 033 551 02 89 በመጠቀም መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

