ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
59

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ የሚስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 ለምግብ አገልግሎት የሚዉል የተዘጋጀ በርበሬ፣ የተዘጋጀ ሽሮ፣ አተር ክክ፣ ምስር ወዘተ፣ ሎት 2 የእርድ ስጋ፣ ሎት 3 አትክልት፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ እንቁላል ወዘተ እንዲሁም ሎት 4 ማገዶ እንጨት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም  የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ወይም በባንክ በተመሰረተ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  11. ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው፡፡
  12. አሸናፊው በገባው ውል መሰረት እቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ 033 111 46 84 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here