በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ግንባታዎችን በጨረታ በማስገንባት ማለትም፡- ሎት 1 ኪኖ መንደር 2 ቀበሌ የትምህርት ቤት ግንባታ፣ ሎት 2 ሚሊገብላ ቀበሌ የእንስሳት ክኒሊክ ግንባታ፣ ሎት 2 በለስ ቀበሌ የገበሬ ማሰልጠኛ ግንባታ ሎት 4 አበለገዝ ወንዝ እስከ ሎማ ቀበሌ የገጠር መንገድ ጥገና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፦
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ከግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገነቡት ግንባታዎችና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ መሆኑም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ በጥንቃቄ መሙላት አለባቸዉ፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ ጥሬ ገንዘብ 2 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከዉድድር ዉጪ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደባርቅ ዙርያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ድረጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስክበርያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ይሁን እንጅ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ22 ተኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የሥራ ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ400 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የግንባታዉ የርክክብ ቦታዉ ሳይቶች የግንባታ ሥራ ተሰርቶ ሲያልቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቻውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም ስልክ ቁጥር 058 117 00 11 ወይም በፋክስ ቁጥር 058 117 04 21 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

