የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ለቢሮ ጥገና የሚውሉ እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመሰከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በሎት የሚገዛውን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማገኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ስፔስፊኬሽን ሳይሞላ ክፍት ያደረገ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት በሎት ዘርዝሮ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎት የተዘረዘረውን ሁሉንም ሳይሞላ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ፍርድ ቤቱ በአጠቃላይ እንዲገዛ ካዘዛቸው እቃዎች ላይ 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ፍርድ ቤቱ ተጫራቾችን በእያንዳንዱ ሎት በተናጠል ዋጋ የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደረበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 02/2018 ዓ.ም በ20 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ጥር 03/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በኋላ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የሥራ ሂደት 3፡00 በኋላ ይከፈታል፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች እብናት ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊዎች እንደስፈሳጊነቱ ለ6 ወር ኩንትራት ውል አገልግሎት ሊወስዱ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸነፊ መሆን የሚችለው በየአንዳንዱ ሎት በተናጥል ዋጋ ዝቅተኛው የዋጋ መጠን የሞላ ነው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ ከተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) እና በናሙናው መስረት መሆን አለበት፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 00 32 /058 440 01 23 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት

