በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመደበኛ በዉስጥ ገቢ እና Susan Thompson Buffet Foundation የበጀት ምንጭ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎችን እና ግንባታ ጥገና በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ አይነት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የደንብ ልብስ፣ ሎት 4. የኤክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 የመኪና ጎማ፣ ሎት 6. የግንባታ ጥገና (የበርና የመስኮት ፣መስታዉት ፣ ዉሃ ዝርጋታ፣ የማዋለጃ ክፍል፣ አልሙኔም ፓርቲሽን ፣የዉጭ የግድግዳ የቀለም እድሳት ፣የቆርቆሮ የቀለም እድሳት የተሰባበሩ በርና መስኮት እድሳት፣ የኤሌክትሪክ መብራቶች ጥገና፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸዉ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክሲ (ቫት) ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን እያንዳንዱን መግዛት የሚፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት የሚነበብ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታዉ ሰነድ የሚሸጠዉ ጨረታዉ ከወጣበት ታህሳስ 13/2018 እስከ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ቆይታ ይኖረዋል፡፡
- ጨረታዉ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት የእቃ አይነት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) እና የግንባታ ጥገና ለሚወዳደሩ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለበት እና በጨረታዉ ላይ ስማቸዉን ፊርማቸዉንና የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ጨረታዉ የሚታየዉ በሎት ስለሆነ ከጨረታ ሰነዱ ያሉትን ሁሉንም እቃዎች መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት የጨረታ ሰነዶች በኦርጅናል እና በኮፒ ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረዉ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በየሎቱ የጥቅል ዋጋዉን አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጥሬ ገንዘብ ሆነ ቸክ አይይዞ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ከዉድድር ዉጭ ያደርጋል፡፡
- በሎት 7 የቀረበዉ የግንባታ ጥገና ተሳታፊዎች ደረጃ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም የግንባታ ጥገና ዋጋ ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እና የእጅ ዋጋዉን ያጠቃልላል፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ጥገና ዉል እንዲወስድ በተጠየቀ ጊዜ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ፊት ቀርቦ ዉል መዉሰድ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዳባት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

