በሰሜን ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የአዴት ከተማ አስ/ገን/ ጽ/ቤት ለአዴት ከተማ አስተዳደር ለመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፤ ሎት1. ቀበሌ 03 ቢሮ አካባቢ የሚገኝ የአረንጓዴ ልማት ግንባታ ሥራ AM/Adet/CIP/CW-02/2526፣ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ የፕሮግራሙ በጀት AM/ADET-CIP-G-01/25/26፣ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በፕሮግራሙ በጀት AM/ADET-CIP-G-01/25/26፣ ሎት 2 የቤትና የቢሮ እቃዎች በፕሮግራሙ በጀት AM/ADET-CIP-G-01/25/26 እና ሎት 3 በመደበኛው በጀት የሚገዙ የጽህፈት መሳሪያና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለአረንጓዴ ልማት ግንባታ ሥራ ደረጃ ሰባት እና በላይ ያላቸው፡፡
- የደረጃ ምዝገባና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዉን ወይም የፕሮጀክቱን ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለፕሮጀክት ግንባታ አረንጓዴ ልማት 21 ቀን ለእቃ 15 ቀን የሚውል መሆኑንና በአዴት ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የፕሮጀክት ግንባታ ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ ቀበሌ 03 ቢሮ አካባቢ የሚገኝ የአረንጓዴ ልማት ግንባታ ሥራ AM/Adet/CIP/CW-02/2526 ሎት 1 ብር 170,000 (አንድ መቶ ሰባ ሽህ ብር) የጽህፈት መሳሪያ የፕሮግራሙ AM/ADET-CIP-G-01/25/26 ሎት 1 ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር) የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በፕሮግራሙ AM/ADET-CIP-G-01/25/26፣ ሎት 2 21,000 (ሃያ አንድ ሽህ ብር) የቤትና የቢሮ እቃዎች በፕሮግራሙ የሚገዙ AM/ADET-CIP-G-01/25/26፣ ሎት 3 11,000 (አስራ አንድ ሽህ ብር) እንዲሁም በመደበኛው በጀት የሚገዙ የጽህፈት መሳሪያና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በሞላዉ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ቢድ ቦንድ) (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የዋጋ መሙያ ፎርሙን በመሙላት በፖስታ በማሸግ በአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት በግዥና ፋ//ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለፕሮጀክት በ22ኛዉ ቀን ለእቃ በ16 ተኛው ቀን እስከ 3፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ለፕሮጀክት በ22ኛዉ ቀን ለእቃ በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ከሆነ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ግንባታ ወይም እቃ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፡፡ ዋጋ ለይቶ መሙላት አይቻልም፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ወይም የሚሰራዉ የፕሮጀክት ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆኑ በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ /ባለሙያ/ ተረጋግጦ የምንረከብ መሆኑንና ልዮ ሙያ የሚጠይቅ ከሆነ በቴክኒካል ባለሙያዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደ ሁኔታው አይቶ የሎት ግዥን ለእቃ 20 በመቶ የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ለፕሮጀክ እና ለእቃ 40 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- በከተማችን የፕሮጀክት ሥራ ዉል ወስደዉ ሳያጠናቅቁ ያቋረጡትን አይጋብዝም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 338 00 43 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ግዥዉ በመመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በመመሪያ ማሻሻያ በራሪ ጽሁፎች እንዲሁም በ15/09/2014 ዓ.ም በወጣዉ የግንባታ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ማሣሰቢያ፡- እኛ ከሸጥንላችሁ ሰነድ ውጭ በራሣችሁ ቅጽ መሙላት፣ በፍሉድ ማጥፋት፣ ሥርዝ ድልዝ፣ በራስ ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙላት፣ ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት እና የድርጅት ማህተም ያላደረገ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
አዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት

