በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ማቴሪያሎችን በድምር (ሎት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 5 ደንብ ልብስ በየ ሥራ ዘርፋቸው ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊዎቹ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተሰጣቸው፡፡
- ማንኛውንም የሚጠየቁትን መረጃ ማሟላት የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆኑ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ አይተም ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ግልጽ ጨረታ በ16 ተኛው ቀን ኦርጅናሉን በማስገባት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት 5፡00 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረብ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መፈጽም ይኖርባቸዋል፡፡ ሥራው ከተጠናቀቀ እና ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀን ፀንቶ ይቆያለ፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 18 49 45 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ሁሉም ተጫራች 15 በመቶ (ቫት ) ተመዝጋቢ መሆን አለበት፤ አሸናፊው እቃውን በራሱ ወጭ ሆስፒታል ድረስ ማምጣት አለበት፡፡
የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

