በአብክመ የምስ/ጎጃም የብቸና መረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ እንዲሁም የመኪና ጎማ እና የተለያዩ የምግብ አቅርቦት ከመደበኛና ከውስጥ በጀት መግዛት ይፈልጋል፡፡ሎት1.ጤፍ፣ ሎት2.በቆሎ ፣ሎት3. አተር እና ጓያ እንዲሁም ጎመንዘር ፣ ሎት4. በርበሬ፣ ሎት5. ቅመማ ቅመም ፣ ሎት6. ፊኖ ዱቄት ፣ ሎት7. ስኳር እና ዘይት እንዲሁም የዳቦ እርሾ እና ፓውደር፣ ሎት8. የምግብ ጨው፣ ሎት9. አትክልት እና ፍራፍሬ ሽንኩርት እና ቃሪያ ሎት10. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት11. የጽ/መሳሪያ ፣ ሎት12. የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ የሚያቀርቡ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከተጨማሪ እሴት ታክስ ግዴታ ተመዝጋቢዎች ውጭ የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዝጋቢ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው ፤ለሁሉም ሎቶች ከጨረታው አሸናፊ ላይ ሁለት በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡
- ለሁሉም ሎቶች ጨረታ ሲሞሉ ህጋዊ ማህተም እንዲሁም ፊሪማ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ፓስታው ላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመያዝ ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ብቸና ማረሚያ ቤት የፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ለሎት1. እስከ ሎት9. 3,000 (ሶስት ሺብር) ፣ለሎት10. 17,000 (አስራ ሰባት ሺ ብር)፣ ለሎት11. 1,500 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) ሎት12. 3,000 (ሶስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ -1 ገቢ በማድረግ ኮፒውን ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ከሎት 1 እስከ 12 ላሉ ግዥዎች አሸናፊቱ ከተገለፀበት ቀን በ’ኃላ ለውል ማስከበሪያ 10በመቶ ዋስትና በጥሪ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከሎት 1 እስከ ሎት 12 ያሉ ሎቶች ተጫራቶች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፓስታ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ለሁሉም ሎቶች ጨረታው ሲከፈት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
- ከሎት 1 እስከ ሎት 12 በጨራታ ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም ካለም ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
- በባለሙያ የሚረጋገጡ ዕቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጠ የምንረከብ መሆኑን እና አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ብቸና ማረ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቶች በየሎቱ ምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ ወይም ውድቅ ይሆናሉ፡፡
- ከሎት 1 እስከ 3 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀይር ከዕቃው ከጠቅላላ መጠን ላይ 20በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እነ/ወ/አቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
- ከሎት 1 እስከ 3 የሞሉትን ዋጋ ኦርጅናሉን እና ሲፒኦ ብሎ በማሸግ በተጨማሪ ግልፅ በሆነ መልኩ የሞላበትን ቀበሌና ጎጥ መፃፍ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ከሎት 1 እስከ 3 ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ30 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ፣የጨራታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በማጠቃለያ ፓስታ በማሸግና በፐስታው ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ዋጋ መሙላት ሲኖርባቸው በራሱ ዋጋ መሙያ ከሞላ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 11 49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የብቸና ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት

