በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት በተያዘ በመደበኛ በጀት አይንባ መቋሚያ ቀበሌ ላይ አዲስ መንገድ ግንባታ ሥራ ማሽን ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በነፃ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከታህሳስ 20/2018 ዓ/ም ጀምሮ ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የምንከራየው ማሽን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየው በሎት ድምር በቀረበዉ ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ተጫቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 4/2018 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ከጨረታ ሰነዱ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 5/2018 ዓ/ም በ3፡30 በግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን ታህሳስ 5/2018 ዓ.ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
- ሎቢድ ደርሶ መልስ እና ነዳጅ በአሸናፊው የሚሽፈን ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ቀርቦ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክኒያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

