ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ለመሰብሰቢያ አገልግሎት የሚውል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ደረጃ 7 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 ህንጻ ሥራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በማሰራት ዋጋ ከሞሉት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት (bill of quantity) በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት ከገንዘብ ያዥ ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/አ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጉ በ4፡00 ይከፈታል እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም ከኢንሹራንስ የሚሰጥ ዋስትና በምዕ/ጎጃም/ዞ/ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ የሚችል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here