ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የቻግኒ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት  በሆስፒታሉ ግቢ ዉስጥ የዉስጥ ለዉስጥ መንገዶችን በሎት 1 ኮብል ንጣፋ እና በሎት 02 ክፍሎችን ማስፋፍያ እና ጥገና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከተቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቸቻው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የስራዉ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የእለት ገቢ ስብሳቢ ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ለሚወደደሩበት ሥራ  ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከሆስፒታላችን ግቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ በማሽግ ማሰያዝ አለበችሁ፡፡ ነገር ግን የጨረታ ማሰከበሪያ በቼክ ካሰያዙ ከውድድር ውጭ ያስደረጋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ሰነዱን በመሙላት ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በአንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሽግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግ/ፋ/ን/አስ/ዳ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ውስጥ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሰይ ሰዓት ተሸጎ በተመሳሰይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን ሥራ  በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ጨርሶ የማሰረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
  13. ውድድሩ በሎት (ጥቅል) ድምር መሆኑን አውቀው የተጠየቁትን የስራ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉልን እንጠይቃለን፡፡
  14. ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 556 20 09 ወይም ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የቻግኒ መጀመሪያ ደረጀ ሆስፐታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here