በድጋሚ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

በሰሜን ጎንዳር ዞን የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዳባት ወረዳ ለሁሉም መኪናዎች  ዓመታዊ የመኪና  መለዋወጫ  ዕቃ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚሟላሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የ2018 ዓ.ም የዘመኑን የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ የ2017 ዓ.ም የታደሰዉ እስከ ታህሳስ 30/2018 የሚያገለግል መሆኑን የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ፤
  5. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  6. ጨረታው ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚገዙበት ዋጋ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ  ብር) ብቻ ዳ/ወ/ግ/ፍ/ን/አስ/ድጋፊ የስራ ሂደት  ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የመለዋወጫ ዋጋ 3 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ  ፖስታ አጠቃሎ በማሸግ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 4/2018 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23  በቀን  ጥር 05/2018 ዓ/ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/እስ/ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23  ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 02 05 ወይም 058 113 04 10 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
  13.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14.  የጨረታው መክፈቻ ቀን ብሔራዊ በዓል ቀን እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡

የመኪና ስፔሩ (ድርጅቱ) የምናስጠግንበት ማዕከላዊ ጎንዳር ከተማ  ማዕከል መሆን አለበት፡፡

የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here