ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
35

የግዥ መለያ ቁጥር መ/ግ/004/2018 ዓ.ም

በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃበት ልማት ቢሮ እና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለአገልግሎት የሚውሉ የ2018 በጀት አመት የአላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች ጥቅል ግዥ ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. የፕሪንተር፣ የፎቶ ኮፒና የፋክስ ማሽን ቀለሞች (ቶነሮች)፣ ሎት 3.የመኪና ዲኮር (ጌጣጌጥ) እና የታፒሴሪ ዕቃዎች፣ ሎት4. የጽዳት እና መዋቢያ ዕቃዎች፣ ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ፣ ሎት6. የሕንፃ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ሎት7. የፈርኒቸር (የቤትና የቢሮ ዕቃዎች)፣ ሎት8. ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ ከነ ካላማዳሪው፣ ሎት9. የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች  የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ  የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1 – 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ( ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለዕቃዎች ግዥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ  በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃበት ልማት ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት 8፡00  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር  007 በ16ኛው ቀን 8፡00  ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11.  ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 / 0582209646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃበት ልማት ቢሮ (ፑል)

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here