በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥና ፋይናንስ አስ/የሥ/ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንፅህና መጠበቂያዎች እና የፅህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቀረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ሓይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ግዥና ፋ/ ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጀት ግፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከሞቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
- የንጽህና መጠበቂያ እና የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
- የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች አሸናፊው የሚለየዉ በተናጠል ዋጋ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎቹን ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በክፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 10 65 ወይም 033 222 04 83 ደዉሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

