ለመጀመሪያ  ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
38

በአብክመ በባሕርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኙው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ግዥ ለሶለተኛ ጊዜ፣ ሎት 2. ፈርኒቸር ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት 3. የመኪና ጎማና መለዋወጫ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 4. የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት 5. የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 6. የጽዳት እቃዎች ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት 7. የህትመት የአገልግሎት ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ ሎት 8. የአገለገሎ ዕቃዎች ሽያጭ ለሁለተኛ ጊዜ ሎት 9. ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነ መጋዘን ለማሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ሎት 10. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ እና ሎት 11. የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓረት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ በጋዜጣ አወዳድሮ ከአሽናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ፣ የሚገዛውን መግዛት፣ የሚሰራውን ማስራት እና የሚሸጠውን መሸጥ ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡትን 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጡትን ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁለተኛና ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7 ተኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፡፡ በ7 ተኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለመጀመሪያ  ለወጣው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡ አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
  12. ሰብል ማጓጓዝ የመርክበ ኃላፊነት የዩኒየኑ ወይም የመሰረታዊ ህ/ስ/ማህበሩ የሚወክለው ንብረት ክፍል ሲሆን የማስጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊ ትራንስፖርተር አይከፍልም፡፡ የትራንስፖርት ማጓጓዣ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች አሸናፊ ትራንስፖርተር ይሸፍናል፡፡
  13. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት በኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ ማራገፊያው ድረስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡ የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርተ ጨረታ የሚፈለጉትን ማህበር መርጦ መሙላት ይችላሉ፡፡
  14. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአራት ወር የሚቆይ ሁኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህ እና በላይ የሆነ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡ የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋሚ የሚሞላው የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት*ቁመት*ወርድ-15%/1.8*10= መጋዝን የመያዝ አቅም ስለሚሰጥ የተሞላው የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን የመጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሜቴ ተለክቶ በሚገኘው መሰረት ይሆናል፡፡ የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሁኖ አሸናፊውን በቅድም ተከተል ይሚያዝ ይሆናል፡፡
  15. አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 08 26 26 /09 11 59 05 34 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here