ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
48

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በCIP በጀት የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ለሚያሰራው የተለያዩ መሰረተ ልማቶች 1. ሎት 1 የኮብል መንገድ ግንባታ ቀበሌ 02 ከአቶ መኩሪያ ተሾመ መኖሪያ ቤት እስከ አለልኝ አድማሴ ቤት ድረስ፣ 2. ሎት 1 የጠጠር መንገድ ግንባታ ቀበሌ 02 ከወ/ሮ ፀጋየ አዳል መኖሪያ ቤት  እስከ ዛንጢ ችግኝ ጣቢያ ድረስ እና ሎት 2 የጠጠር መንገድ ቀበሌ 03 ከዋናው አስፓልት እስከ ወንድም አሻግሬ መኖሪያ ቤት  የግንባታ ሥራዎች የተጫራቾች ደረጃ GC፣ RC ደረጃ 6 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የሚያቀርቡ፡፡
  3. ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የታደሰ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በመንገድ ሥራዎች ልምድ ያላቸው ሆኖ በመንገድ ሥራዎች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 የኮብል መንገድ ብር 165,000 (አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሽህ ብር)፣ ለሎት 1 የጠጠር መንገድ ስራ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) እና ለሎት 2 የጠጠር መንገድ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማስገባት አለባቸው ፊርማ፣ ሙሉ ስም፣ የድርጅቱን ማህተም፣ የተጫረቱበትን የሥራ ዓይነት ከፖስታው ላይ አድራሻቸውን በመፃፍ በነ/መ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለግንባታ ግዥ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያግድ ነገር የለም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን (ካላንደር) ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ አይችሉም ጨረታውን ለማዛባት ወይም ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው ይወረስና ለወደፊቱ በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  12. ጨረታው የሚለየው በሎት (በጥቅል ዋጋ) በመሆኑ ዋጋውን ሲሞሉ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡
  13. የሚሰሩ ሥራዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ጨረታውን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ፈጽሞ የተከለከለ ነው ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  16. በአንዱ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋው መካከል የዋጋ ልዩነት ቢኖር የአንዱ ዋጋ ገዥ ይሆናል፡፡
  17. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ከሆኑ የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ለጽ/ቤቱ በአድራሻ የተጻፈ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  18. አንድ ተጫራች ከአንድ የጨረታ ሰነድ ውጭ መግዛት አይፈቀድም፡፡
  19. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 እና መሻሻያዎቹ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 74 ወይም 058 445 02 58 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here