በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጭልጋ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የመኪና ጎማና ባትሪ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 5 አላቂ የመኪና መለዋወጫ እቃ እንዲሁም ሎት 6 የመብራት ጀኔሬተር እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉ በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ቢሮ ቁጥር 7 ከረዳት ገ/ያዥ ድረስ በመምጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦዉን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸዉንና አድራሻቸዉን በመፃፍ በጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፖስታዉን እስከተገለፀዉ ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ዉስጥ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዎች የሁሉም ምድብ ዕቃዎች የሚያቀርቡት በጭ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለዉድድር ከቀረቡ በኋላ ሀሳባቸዉን መለወጥ ማሻሻል ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጨረታዉ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለዉ ጨረታዉ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉን የምንለየዉ በጥቅል ድምር ወይም በተናጠል ይሆናል፡፡
- ናሙና የሚያስፈልጋቸው የዕቃ በናሙናው መሰረት የሚቀርብ መሆኑንና እቃው ናሙና በጭ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 የሚገኝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሁሉንም አይተሞች መሞላት አለባቸዉ ክፍት መሆን የለበትም፡፡ እንዲሁም በየገፁ የድርጅትዎ ማህተምና ፊርማ ይደረግበት፡፡
- ለበለጠ መረጃ ከግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 11 57 /09 18 43 38 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

